ሀገሬ ቲቪ

እንግሊዝ ከአፍሪካ የሚገቡ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ አደረገች

እንግሊዝ ከታዳጊ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያስችላት ዘንድ ከነዚሁ ሀገራት የሚላኩ ከመቶ በላይ የተለያዩ ምርቶች ሳይቀረጡ ወደ ሀገሯ እንዲግቡ ፈቀደች።

እንዲህ አይነቱ እርምጃ እንደ አፍሪካ ያሉ ታዳጊ ሀገራት ከእርዳታ ጥገኝነት እንዲላቀቁ ለማስቻል እንደሆነ እንግሊዝ አስታውቃለች። 65 የተለያዩ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የዚህ እድል ተጠቃሚ ይኾናሉ ተብሏል።

99 በመቶ ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ምርቶች ምን አልባትም ከአፍሪካ ሀገራት ሊኾን እንደሚችል ተጠቁሟል።በእንግሊዝ በሰፊው የማይመረቱ እንደ ልብስ፣ ጫማና ምግብ ያሉ ሸቀጦች በዝቅተኛ ወይም ዜሮ የግብር መጠን ወደ ሀገሪቱ ይገባሉ።

በሙሉጌታ በላይ
2022-08-17