ሀገሬ ቲቪ

በቻይና ፋብሪካዎች ለስድስ ቀናት እንዲዘጉ ታዘዘ

በቻይና ሲቹዋን ግዛት የሙቀት መጠን በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት በግዛቱ ያሉ ፋብሪካዎች ለስድስት ቀን እንዲዘጉ ታዘዘ።በሙቀት መጨመሩ ሳቢያ የኀይል መቆራረጥ እና እጥረት በመከሰቱ ነው ፋብሪካዎች ሥራቸውን እንዲያቆሙ የታዘዙት።

የሲቹዋን ግዛት የአለማችን ግዙፍ ኤሌክትሮኒክስ አምራች ከኾነው አፕል ጋር በጋራ የሚሰሩ ድርጅቶች የሚገኙባት እና የሶላር ኃይል ምርቶችን በማምረት የምትታወቅ ናት።

ቻይና በስድስት አሥርተ ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀው ከፍተኛ ሙቀት አጋጥሟታል። ከ 10 በላይ ከተማዎች የሙቀት መጠኑ ከ 40 ድግሪ ሴልሲየስ በላይ ኾኖ ተመዝግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-08-17