ሀገሬ ቲቪ

እርጅናን ለመርመር ወደጠፈር የተላከው የሰውነት ክፍል

የእርጅና ሚስጥሮችን ለመመርመር የሰው የጡንቻ ሴሎች ወደህዋ ተላኩ፡፡ በጥናቱ የሰው ሴሎች እንዴት በዝቅተኛ ስበት ውስጥ እንደሚያረጁ ለማጥነት በስፔስ ኤክስ መንኮራኩር ተልከዋል፡፡ መንኮራኩሩ በፍሎሪዳ ከኬኔዲ የጠፈር ማዕከል በላብራቶሪ እንዲያድጉ የተደረጉ የሰው ሴሎችን ይዞ እንዲመጥቅ ተደርጓል፡፡ ጠፈርተኞች ዝቅተኛ ስበት ባላቸው ከባቢዎች ወደመሬት ተመልሰው ከማገገማቸው አስቀድሞ የእርጅና አይነት የጡንቻ መድከም ያጋጥማቸዋል፡፡ ማይክሮ ኤጅ የተሰኘው ጥናት በዝቅተኛ ስበት ከባቢ ውስጥ የሚኖረውን የጡንቻ ሴሎች ለውጥ ከዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሚያጠናም ነው፡፡ ጥናቱ የእርጅና ሂደት ምን ያክል በጡንቻዎች እና አጥንቶች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ለመረዳት እንደሚያስችል ተመራማሪዎች ተስፋ ጥለውበታል፡፡ በተጨማሪም ለምንድነው እርጅና ጡንቻዎች እንዲደክሙ የሚያደርገው የሚለውን ለመረዳት ብሎም የጡንቻ መድከሙን የመከላከል አማራጮችን ለመፈለግ ያስችላል ተብሏል፡፡ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት የሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከጠፈር የሚመለሰውን ናሙና መሬት ካለ ናሙና ጋር በንጽጽር ያጠናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-23