
የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ መሪዎች 42ኛ ጉባኤያቸውን በኪንሻሳ ጀምረዋል። በጉባኤው የሀገራት ትስስርን እና የአካባቢ ንግድን በማጠናከር ረገድ የተገኘው ውጤት ይገመገማል ተብሏል ።
የአካባቢ ሰላም ፤ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፣ የማዕድን ሀብት ማበልጸግ እና ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት በስፋት እንደሚመከርባቸው ተገልጿል ።በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይም ማላዊ የአመራር ቦታውን ለተረኛዋ ኮንጎ እንደምታስረክብ ተሰምቷል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-18