በአውሮፓ በተከሰተ ድርቅ ሳቢያ እንደ ጀርመን ያሉ አንዳንድ አገሮች ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የባቡር ትራንስፖርትን እየተጠቀሙ መሆኑ ተሰምቷል ።
ቁሳቁሶቹ ከዚ ቀደም በባህር ትራንስፖርት የሚጓጓዙ ሲሆን አሁን ላይ በአህጉሪቱ የሚገኙ ወንዞች በድርቁ ሳቢያ መጠናቸው በመቀነሱ ፊታቸውን ወደ ባቡር ለማዞር ተገደዋል ።
ጀርመን የአውሮፓ ሀገራት ለሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡትን ትኩረት ገታ አድርገው ይህን አስደንጋጭ ክስተት መዋጋት አለባቸው ስትልም አሳስባለች ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-18
