ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካና ታይዋን ስምምነት

አሜሪካና ታይዋን ግንኙነታቸውን ሊያጠናክር የሚችል የንግድ ውይይት እንደሚጀምሩ አስታወቁየአሜሪካ የንግድ ተወካይ ለውይይት በተቀመጡ ሃሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ዙር ውይይት በሁለትና በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄደም ይፋ አድርገዋል።

አሜሪካ ከታይዋን ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ በ2020 106 ቢሊየን ደርሶ ነበር።ይሁን እንጂ ታይዋን ከቻይና ጋር ውጥረት ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰዐት አሜሪካ የንግድ አጋርነቴን አጠናክራልሁ ማለቷ ውዝግቡን ይበልጥ እንዳያከረው ተሰግቷል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-18