የሩሲያ የዩክሬን ጦር መማዘዝ ዳፋው በየሁሉም ሀገር ደጃፍ ደርሷል ማልት ይቻላል። በጦርነቱ ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት አድርጓልና።
ዩክሬንና ሩሲያ በድምሩ 30 በመቶ የዓለም ስንዴ ምርትን ያመርታሉ። ከዓለም በቆሎ ምርትም 20 በመቶውን ይሸፍናሉ፡፡ የሱፍ ምርትንም 20 በመቶ ድርሻ የያዙት እነዚህ ሁለቱ አገሮች ናቸው፡፡
ሩሲያ ከስንዴው በላይ ደግሞ የዓለማችን ግንባር ቀደም የሰብል ማዳበሪያ አምራች ሀገር ስትሆን፣ በዓመት ሰባት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የማዳበሪያ ምርት ወደ ውጪ ትልካለች። ለዚህ ነው የሁለቱ ሃገራት ጦርነት የሁሉንም በር ያንኳኳነው የሚባለው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከድርቅ ጋር ተደማምሮ በአፍሪካና በሌሎች በኢኮኖሚ ባላደጉ ሀገሮች 47 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ላይ የረሃብ አደጋተጋርጧል ብሏል።
ጦርነቱ እና የታገደው የምግብ ወጪ ንግድ የስንዴን ገበያ 25 በመቶ እንዲያሽቅብ ሲያደርገው የማብሰያ ጋዝ፣ የምግብ ዘይት እና የማዳበሪያ ዋጋም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋውቸው የማይቀመሱ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
ባለፈው ወር ዩክሬን የእህል ምርቷን በጥቁር ባህር በኩል ወደ ሌሎች ሀገራት መላክ የሚያስችላት ስምምነት ከሩሲያ ጋር በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል ተፈራርማ ነበር።
ሩሲያ እና ዩክሬን ስምምነቱን የፈረሙት በቱርክ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አደራዳሪነት እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል።
በስምምነቱ መሰረትም እስካሁን 25 የሚደርሱ እህል የጫኑ መርከቦች ከሩሲያ እና ዩክሬን መውጣታቸው ተነግሯል ።
ወደ ውጪ ለመላክ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት በተለይም በድርቅ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ፣ በአንበጣ መንጋ ወረራ እና በዩክሬን ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው የአፍሪካ ቀንድ አገራት ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከተባበሩት መንግስታትን ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ከተርክዬ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር የዩክሬን እህል ወደ ውጭ መላክን የተደረሰው የ120 ቀን ስምምነት ለማስቀጠልና አፈጻጻሙን ለመገምገም ይገናኛሉ ተብሏል።
ዩክሬን ሩሲያ ከስምምነቱ በተጻራሪ ዋነኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዬን ተቆጣጥራለችና እሱም ላይም ምክክሩ መፍትሔ ሊያምጣልኝ ይገባል እያለች ነው።
የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጉተሬዝ ወደ ዩክሬን የሚያደርጉት ጉዞ “በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ከምግብ ቀውሱ ጋር በተያያዘ በእጅ የሚዳሰስ ለውጥ ያስገኛሉ ብለዋል።
የተርኪዬ ፕርዝደንት ፅህፈት ቤት ኤርዶጋን በዲፕሎማሲያዊ መላ ስለ እህል ስምምነቱና ጦርነቱን መቋጨትን በተመለከተ ጥረት ያደርጋሉ ብሏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-18
