ሀገሬ ቲቪ

መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

መንግስት የስኳር ፋብሪካዎችን ወደግል ለማዘዋወር ባወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።

ለጨረታ የቀረቡት ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3 ፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ አርጆ ደዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ የስኳር ፋብሪካዎች ናቸው ተብሏል።

ጨረታው ተወዳዳሪነትን እና የስኳር ምርታማነትን ከማሳደግ አልፎ ኢትዮጵያ ለስኳር ግዢ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት፥ ገቢን ለማሳደግ ብሎም የሸንኮራ አገዳ አምራቾችን ህይዎት ለማሻሻል እንደሚረዳ የገንዘብ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመላክቷል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-19