ስፓይደር ማን ኖዌይ ሆም የሚለው አዲስ ፊልም ክብረወሰንን አስመስግቧል መባሉን ሰምተናል። ፊልም ለብዙዎቻችን የእረፍት ጊዜያችንን የምናሳልፍበት የመዝናኛ አማራጫችን ነው። በኮቪድ ወረርሽኝ ሳቢያ በእጅጉ ተጎድቷል ከተባሉት ዘርፎች መካከል አንዱ የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ነው። ታዲያ ዓለም በወረርሽኝ በተጨነቀችበት በዚህ ወቅት ፊልሙ አንድ ቢሊዮን ዶላር መሰብሰብ ችሏል። ፊልሙ በዓለም አቀፍ የደረጃ ሰንጠረዥ ቦክስ ኦፊስ ላይ ከአናቱ በመቆናጠጥ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሰራ የመጀመሪያው የወረርሽኝ ጊዜ ፊልም ሆኗል። በዓለም ዓቀፉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተመዘገበው እንደ ምዕራባውያኑ በ2019 ነበር። የኮቪድ ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የሲኒማ ኢንዱስትሪው ከ1ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲያስገባ ይህ የመጀመሪያው ነው። ፊልሙ የ2021 ከፍተኛ ገቢ ያስገኘ ፊልምንም ማዕረግን ወሰዷል።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-27
