ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው

አሜሪካ ለዩክሬን 800 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለታደርግ ነው። ሮይተርስ ከታማኝ ምንጮች ሰማሁት ብሎ እንዳስነበበው የባይደን አስተዳደር በርካታ የጦር መሳርያ ከአሜሪካ የክምችት ቋት ወጥቶ እንዲሰጥ ወስኗል።

ይህንንም በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርገው ተዘግቧል። የኋይት ሀውስ ሰዎች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመሰጠት ተቆጥበዋል።

በእስካሁኑ የጦርነት ሂደት አሜሪካ ለዩክሬን ከቀላል እስከከባድ የጦር መሳርያ ድጋፍ ማድረጓ ይታወቃል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-19