ተቋማት ለአደጋ ግዜ ምላሽ የሚሰጡ አጭር የስልክ መቀበያዎችን ለዜጎች ያዘጋጃሉ ። በእኛም ሀገርም አጭር የስልክ ቁጥሮች ያሏቸው ተቋማት በርከት ያሉ ናቸው።
ተቋማቱም ዜጋውም በአግባቡ ይጠቀመዋል ወይ ሌላ ጉዳይ ቢሆንም ። ከሀገራችን የአደጋ ስልክ ቁጥር በላይ እናውቀዋለን 911
ወደ እዚህ የጥሪ መቀበያ እንደተደወለ ሰማን ።
ነገሩ ያስገረመን መደወሉ አይደለም ። አንድ እንስሳ መደወሉ እንጂ ።
ከወደ ካሊፎርኒያ አንድ ዝንጀሮ ለአደጋ ጊዜ ጥሪ ምላሽ በሚሰጠው በ911 ደውሎ ፖሊስ እንዲመጣ አድርጓል ። ፖሊሶች ጥሪ እንደደረሳቸው ስልኩ እንደተቋረጠም ይናገራሉ።
ቁጥሩን መልሰው ለመደወል እና የጽሑፍ መልእክት ለመጻፍ ቢሞክሩም ምላሽ ባለማግኘታቸው ጥሪውን ለማጣራት በሚል የፖሊሶች ቡድን ወደ ተድውለበት ስፍራው ይላካል።
የተደወለበትን ሲያጣሩ ፓሶ ሮብልስ አቅራቢያ ወደሚገኘው የእንስሳት መካነ አራዊት ነው የመራቸው ። የአራዊት ጠባቂዎችም ፖሊሶቹን ሲያዩ በመደናገጥ እነሱ እንዳልደወሉ ማስረዳቱን ተያያዙት ።
በመጨረሽም ራውት የተባለው በመካነ አራዊቱ የሚኖር ዝንጀሮ ጥሪውን እንደአደረገ ደርሰውበታል። ነገሩ እንዲህ ነው የሞባይል ስልክ በግቢው ተጥሎ ነበር።
ራውትም ስልኩን ያገኝ እና በእሱ መጫወት ይጀመራል። በዚህ ሂደት ነው እንግዲህ ንክኪው 911 ሆኖ ዝንጀሮው ወደ ፖሊስ እንዲደውል ያስቻለው።
ፖሊሶቹም ስልኩን መንካቱ ሳይሆን የቁጥሮቹ ጥምረት ትክክል መሆናቸው ነው ያሰገረመን ብለዋል። በዚህ ክስተት የተገረሙት ፖሊሶች በማኅበራዊ ትስስር ገጽ አለም ይገረምበት ሲሉም አጋርተዋል ።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-22
