ሀገሬ ቲቪ

ራኢላ ኦዲንጋ ይግባኝ ጠየቁ

በኬንያ ምርጫ እጩ ተፎካካሪ የነበሩት ራኢላ ኦዲንጋ ውጤቱን ባለመቀበል ለሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አስገቡ።

ራይላ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በዊሊያም ሩቶ 50.49 ለ 48.85 መሽነፋቸውን ቢያውጅም ውጤቱን ባለመቀበል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።

ላለፉት አምስት የምርጫ ግዚያት በተፎካካሪዎቻችው የተረቱት ራይላ ከነዚህ ውስጥ ሶስቱን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስዱም በአንዱም ማሽነፍ አልቻሉም።

አሁንም ምርጫው ለመጭበርበሩ በርካታ ማስረጃዎች አሉኝ ቢሉም በፍርድቤት ተቀባይነት አግኝተው ውጤቱ ላይ ለውጥ ያመጣል ወይ የሚል ነው።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-22