ሩሲያ ባለፉት ሶስት ወራት የቻይና ከፍተኛ የነዳጅ አቅራቢ ሀገር መሆኗን መረጃዎች አመላክተዋል።
የሩሲያ የነዳጅ ምርቶች ዋጋቸው በአንጻራዊነት ዝቅ ማለቱ ከተቀናቃኞቿ አንጎላእና ብራዚል ቀድማ በቻይና ይበልጥ ተፈላጊ እንድትሆን አድርጓታል።
የቻይና የጉምሩክ አስተዳደር እንዳስታወከው ከሩሲያ ወደ ቻይና የሚመጣው ምርት የ7.6 በመቶ ከፍ ጭማሪ አሳይቷል።
ሩሲያ በየቀኑ ከ2 ሚሊዮን ቶን በላይ የተለያዩ ምርቶች ጭነት ወደ ቻይና ትልካለች ። ይህም የምዕራብያውያንን ማዕቀብ ለመቋቋም ዕድል ይሰጣታል ተብሏል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-22
