ሀገሬ ቲቪ

የበረራዎች ስረዛ

በዓለም ዙሪያ ከ1 ሺሕ በላይ በረራዎች ተሰረዙ፡፡ 1 ሺሕ 400 የሚሆኑ በረራዎች በዛሬው እለት መሰረዛቸውን የፍላይት አዌር ዴታ ድረገጽ አመላክቷል፡፡ በበረራዎቹ መቋረጥም የቻይና እና የአሜሪካ መዳረሻዎች ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ኤርላይንስ እንደገለጸው የበረራ መስተጓጎሉ ከሰራተኞች በኮቪድ መያዝ እና መገለል ጋር የተያያዘ እንደሆነም ገልጿል፡፡ ሳምንቱ ተጓዞች ለገና በዓል እና ለአዲስ ዓመት ክብረ በዓል በረራዎችን የሚያደርጉበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጥቂት ተጓዦች በኮቪድ የተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ሆንግ ኮንግ ከደቡብ ኮሪያ የሚደረጉ ሁሉንም በረራዎች ለሁለት ሳምንት አቋርጣለች፡፡ እንደፍላይት አዌር መረጃም አብዛኞቹ የበረራ መሰረዞች በቻይና ድርጅቶች የተደረጉ ናቸው፡፡ የቤጂንግ እና ሻንጋይ አየር ማረፊያዎች ክፉኛ ከተጎዱት ሲሆኑ ወደ 300 በረራዎችን ሰርዘዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-27