የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ አጋር ሴት ልጅ በቦንብ ጥቃት ተገደለች ።
የ 29 ዐመቷ ዳርያ ዱጊን ከሞስኮ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ መኪና ውስጥ ሳለች በተጠመደ ቦንብ ህይወቷ ማለፉን የሀገሪቱ የጸጥታ ሀይል አስታውቋል።
ሟች የፑቲን ቀኝ እጅ በመባል የሚታወቀው የሩስያው ፈላስፋ አሌክሳንደር ዱጊን ልጅ ስትሆን ጥቃቱም አባቷን ኢላማ ያደረገ እንደነበር ተነግሯል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-22
