ሀገሬ ቲቪ

አዲስ የኢንደስትሪ መንደር በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ18 እስከ 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል የተባለውን የኢንዱስትሪ ክላስተር ግንባታ ለማስጀመር የፊርማ ስነስርዓት አካሂዷል ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሚገነባውን የየኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታውን ለመስራት ውል የፈጸሙት ኤም ሲጂ ቲ ኤን ቲ የተባሉ ኮንስትራክሽኖች ሲሆኑ ግንባታውን ከሁለት ዐመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይፈጽማሉ ተብሏል።

በፊርሚያ ስነስርዐቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የ አዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ለከተማ አስተዳደሩ የመጀምሪያ መሆኑን ጠቁመው ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት መጠናከር አለበት ብለዋል ።

ኢንዱስትሪ መንደሩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ ፤ የእንጨትና ብረታብረት ስራዎች ፤ የጨርቃጨርቅና አልባሳት፤ የኮንስትራክሽን ግብአቶች ፤የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፤ የኬሚካልና ፕላስቲክ ውጤቶች ኤሌክትሮኒክስና የመድሃኒት ፋብሪካዎችን በውስጡ የሚይዝ ሲሆን ለሀገር እና ለ ዜጎች በርካታ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል ተብሏል።

የኢንዱስትሪ መንደሩ ግንባታ 21 የተለያየ ወለል ያላቸው ሼዶች እንዲህም 400 የግብዓት አቅራቢዎችና ምርት መሸጫ ሱቆች ይኖሩታል ተብሏል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-23