ሀገሬ ቲቪ

የኦንላይን የቪዛ አገልግሎት

በቀን ከ800 እስከ 1ሺህ 500 የሚደርስ የበይነ መርብ ወይም የኦላይን የቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ ።ይህ የተገለጸው በቆንስላ፣ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በበይነ መረብ የሚቀርቡ አማራጭ አገልግሎቶች ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ የኢሚግሬሽን እና ቆንስላ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ጥራትና ፍጥነትን መሰረት በማድረግ መፈፀም ይገባል ብለዋል።

በበይነ መረብ ቪዛ ለማግኘት ያመለከቱ ደንበኞች በሀሰተኛ ድረገጾች እንዳይታለሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ተብሏል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-08-23