ሀገሬ ቲቪ

ዩክሬን የነጻነት በዓሏን እንዳይከበር አገደች

ዩክሬን የዘንድሮ ዓመት ነጻነት ቀኗን የተመለከተ ክብረበዓል እንዳይደረግ አገደች። በዓሉን የተመለከተ ዝግጅት ቢደረግ ሩሲያ ጥቃት ልታደርስ ትችላለች በሚል ነው ያገደችው።

ዩክሬን ከሶቪየት ኀብረት ተነጥላ የወጣችበትን ዕለት የነጻነቷ ቀን አድርጋ ታከብረዋለች።እገዳው የመጣው የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ የነጻነት በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ሞስኮ መጥፎ ነገር ልትፈጽም ትችላለች ካሉ በኋላ ነው።

በዚህም ምክንያት በዕለቱ በዋና ከተማዋ ኬቭ ማንኛውም ዓይነት የሰዎች ስብስብ ተከልክሏል። የጸጥታ ኃይሎችም ከሩሲያ ሊሰነዘሩ የሚችሉ የፈንጂ እና ሚሳኤል ጥቃቶችን መከላከል እንዲችሉ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል።

ዩክሬን በነገው ዕለት ከሶቪየት ኀብረት ከተገነጠለች 31 ዓመት ይሞላታል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-08-23