ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የአውሮፓ አገሮች የከፋ ድርቅ ሰለባ ከሆኑ ሰነባብተዋል ። አውሮፓ ባጋጠማት ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል ዜጎቿ ለሞት እንዲሁም ለስደት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል።
አህጉሪቱ አሁን የገጠማት ድርቅ በ 500 ዐመታት ውስጥ ገጥሟት ከሚያቀው ሁሉ የከፋ ነው ተብሏል ። እንግሊዝ ወንዞቿ ደርቀዋል ፤ ስፔን የውሃ መጠኔ ከ40 በመቶ በታች ወርዶብኛል ብላለች ፤ ፈረንሳይም ከ7 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን ደኗ በሰደድ እሳት ወድሞባታል። ይህ ሁኔታ ታዲያ አውሮፓን የምትገባበትን አሳጥቷታል ።
በአህጉሪቱ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በያዝነው ዐመት የበቆሎ ምርት በ 16 በመቶ፤ የባቄላ ምርት በ 15 በመቶ፤ የሱፍ ምርቶች ደግሞ የ 12 በመቶ ቅናሽ እንደሚኖራቸውም ተገምቷል።
የዐለም አቀፍ የድርቅ ጥናት ማዕከል በቅርቡ ያደረኩት ዳሰሳ በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛው ወንዞች በከፊል እንደደረቁ ፤ 47 በመቶ የሚሆኑ የ አህጉሪቱ ክፍሎች በተከሰተባቸው የ አፈር እንዲሁም የውሀ መድረቅ ሳቢያ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ እና ሌሎች 17 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከፊታቸው ከባድ አደጋ አደተጋረጠባቸው ታዝቤያለሁ ብሏል።
አሁንም በጣሊያን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በኔዘርላንድ፣ በቤልጅየም፣ በሉክሰምበርግ፣ በሮማንያ፣ በሀንጋሪ፣ በሰሜን ሰርቢያ፣ በዩክሬን፣ በሞልዶቫ፣ በአየርላንድና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ይህ አስደንጋጭ ክስተት እየተባባሰ እንደመጣ የጠቆመው የዐለም አቀፍ የድርቅ ጥናት ማዕከል ድርቁ በዚሁ ከቀጠለም የእህል ምርቶች ባሉበት እንደሚከስሙ ፣ ከቁጥጥር ውጪ የሚሆን ሰደድ እሳት እንደሚበራከትና ፤ በአንዳንድ የአውሮፓ ደቡባዊ ክፍሎች ለብዙ ወራት ሊቆይ እንደሚችል አሳስቧል ሁሉም በቻለው መጠን መረባረብ አለበት ይላል ።
በአህጉሪቱ የውሀዎች መጠን መቀነስ በመጓጓዣ መርከቦች ላይ እያሳደረ ካለው ተጽእኖ በተጨማሪ የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳ በመሆኑ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል 20 በመቶ ቀንሷል ፤ የወንዝ ውኃወችን በመጠቀም የሚቀዘቅዙት የኑክሌር ተቋማትም ገደብ ተጥሎባቸዋል።
ይህ ድርቅ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ካስከተለው የሸቀጦች ዋጋ መጨመር እና እጥረት ጋር ተዳምሮ አህጉሪቱን ለከፋ ችግር ሊዳርጋት እንደሚችልም የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ተንብየዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-08-24
