ምርጫ ቦርድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረብው የሕዝበ ውሣኔ ማደራጀት ጥያቄ ላይ ውሣኔ አሳለፈ።
የፌደሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል የሚገኙ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች አንድ የጋራ ክልል ለመመስረት ወስነው ጥያቄ ስላቀረቡ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ በማደራጀት ውጤቱን ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ ለቦርዱ ማሳወቁ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን የሕዝበ ውሣኔውን ለማደራጀት የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ የጊዜ ሰሌዳ የማዘጋጀው እኔ እንጂ ምክር ቤቱ አይደለም ብሏል።
ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ለማደራጀት እንዲረዳው ዞኖቹ እና ልዩ ወረዳዎቹ ያቀረቧቸውን የውሳኔ እና ጥያቄ ሰነዶች ምክርቤቱ እንዲልክለት ጠይቋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-24
