ሀገሬ ቲቪ

ቻይና ለተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የብድር ስረዛ አደረገች

ቻይና ለ 17 የአፍሪካ ሀገራት የሰጠችውን 23 ከወለድ ነጻ ብድር እንደሰረዘች አስታውቃለች። ሀገሪቱ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2011 ዓ.ም ባሉት 19 ዓመታት ውስጥ የአፍሪካ ሀገራት የተበደሯትን 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ሰርዛለች።

በተጨማሪም 15 ቢሊዮን ዶላር የብድር ለውጥ ወይም ሽግሽግ አድርጋለች። አሁንም ቢኾን ቻይና በአፍሪካ የምታደርገውን የመሠረተ ልማት ግንባታ የገንዝብ ድጋፍ እና ኢንቨስትመንቷን እንደምትቀጥል የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንጊ ተናግረዋል።

ሚንስትሩ ቤጂንግ በዚህ ዓመት ለ 12 የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና እንዲያስገቡ ፈቅደናል ብለዋል። የቻይና ኢንዱስትሪዎች 2 ነጥብ 17 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንት በአፍሪካ አላቸው።

በብሩክ ያሬድ
2022-08-24