ህንድ በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳኢል ተኩሰዋል ያለቻቸውን መኮንንኖች ከስራ አባረረች።
የሕንድ አየር ኃይል እንዳሰታወቀው 3ቱ የወታደራዊ መኮንኖች ተገቢውን ጥንቃቄ ሳይወስዱ ሲነካኩ ነው ሚሳየሎቹ የተወነጨፉት ።
በሩሲያ እና በህንድ እንደተስራ የሚነገርለት ብራህሞስ የተሰኘው ሚሳይል ከ500 እስክ 300ኪሎ ሜትር ርቀት የመምዘግዝግ አቅም የነበረው ነው ።
ህንድና ፓኪስታን አንጻራዊ ሰላም በሆኑበት ወቅት እንዲህ አይነት ስህተት መፈጸሙ ፓኪስታንን ጥርጣሬ ውስጥ ከቷት ይግባኝ ጠይቃ ነበር።
ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ተግባሩ በግዴለሽነት የተከወነ ነው ሲል የአየር ኃይል መኮንኖቹንም ከነጭራሹ ከስራ ሲያባርር ጎረቤት ፓኪስታንንም ይቅርታ ጠይቋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-24
