ሀገሬ ቲቪ

የዓለም ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል

ዓለማችን ኢኮኖሚዋ በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት 100 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ ይሆናል ተባለ፡፡ የዓለማችን ጠቅላላ የምርት ምጣኔ ወይንም ጂዲፒዋ አሁን ካለበት የ5.5 በመቶ ቀንሶ 4.2 በመቶ ይሆናል ይላል ትንበያው፡፡ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በኮቪድ ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም በአየር ንብረት አለፍ ሲልም በ2021 ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የተከሰተው የሸቀጦች፣ ያለቀላቸው እቃዎች፣ የመርከብ ቦታ እና የነዳጅ እጥረት ሳቢያ የተከሰተው የዋጋ ንረት ለመቀነሱ ገፊ ምክኒያቶች ናቸው፡፡ ጥናቱን የእንግሊዙ ሴንተር ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ቢዝነስ ሪሰርች የተባለ ተቋም አጥንቶታል፡፡ አይ.ኤም.ኤፍን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ተቋማት ከዚህ ቀደም የዓለም የምርት መጠን ሊቀንስ እንደሚችል ግምታቸውን ሲያስቀምጡ ነበር፡፡ ታዲያ የዚህ ተቋም ጥናትም ይህንኑ ያረጋገጠ ሆኗል። የዓለም ሀገራት ጠንከር ያለ ማገገሚያ መውሰድ እንዳለባቸውም ጠቁሟል። ዋናው ነገር ዓለማችን የገጠማትን የዋጋ ግሽበት እንዴት እንቋቋመዋለን የሚለው ነውም ብሏል። የዋጋ ግሽበቱ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ 6.8 በመቶ መድረሱን ለማሳያነት አንስቀምጧል። ዓለማችን አሁን ያጋጠማትን የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ካልቻለች በ2023/24 ለመውደቅ እራሷን ማዘጋጀት አለባት ሲል ተቋሙ አስጠንቅቋል።

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-27