የአዲስአበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ትምህርት ዘመን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2015 ትምርት ዘመን እቅድ ላይ ከትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ እንደተገልጸው የ2014 የትምህርት ዘመን በአመዛኙ ጥሩ እምርታዎች የተገኙበት ቢሆንም ተግዳሮቶችም ነበሩበት ።
በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የትምህርት አመራሮች በመማር ማስተማሩ ሂደት አጋጥመን ካሉት ውስጥ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ያለ በቂ ዝግጅት መጀመር የኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ እና መዝሙር በትምህርት ቤቶች መጠቀም ላይ የጋራ አረዳድ አለመኖርን አንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ከሓይማኖታዊ ተግባራት ነጻ ማድረግን የተመለከተውን አንስተዋል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አንዷለም ደቻሳ ለተነሱት ጉዳዮች ማብራርያ ሰጥተዋል። በትምህርት ቤቶች አከባቢም እያተስፋፋ የመጣውን ፡ የንግድ እንዲሁም የመማር ማስተማር ስርአቱን ሊያውኩ የሚችሉ ተቋማትን ተከትሎ ለተነሳው ሀሳብም እንዲህ ምላሽ ሰጥተዋል።
በመድረኩ በ2015 ሰለሚጀምረው አዲሱ ስርዓት ትምህርትም ተወስቷል። አዲሱ ስርአተ ትምህርት ሀገር በቀል እወቀቶችን ፡ የግብረ ገብ ትምህርትን ፡ የሙያ ትምህርቶችን እና ቴክኖሎጂን ያቀፈ መሆኑ ተማሪው ወደ መማር ማስተማሩ ለመሳብ ያስችላል ተብሎ እንደታመነበት ተገልጿል።
የቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አንዷለም ደቻሳ ስርአተ ትምህርቱን ያግዛል የተባለው የአዲስ የመፀሀፍ ህትመትም እየተጠናቀቀ በመሆኑ በቅርብ ቀናት ወደ ስርጭት እንደሚገባ አስታውቀዋል ።
የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየው ከካሪኩለም ውጪ የሆነ አሰራርም በአዲሱ ስርአተ ትምህርት እንደ ሚስተካከል ተጠቁሟል።
አዲሱ የስርአተ ትምህርት እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በእጅጉ ያግዛል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-08-26
