ሀገሬ ቲቪ

በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች ከሕውሐት ወታደራዊ ተቋማ እራሳቸውን እንዲያርቁ መንግስት አሳሰብ

ትግራይ የሚኖሩ ወገኖች የሕውሐት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችውን እንዲያርቁ መንግስት አሳሰብ።

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ባወጣው መግለጫ መንግስት ለሕውሐት ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

በመሆኑም በትግራይ የሚኖሩ ወገኖችንየሕውሐት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችውን እንዲያርቁ መንግስት አሳሰቧል።

ሆኖም አሁንም መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-08-26