የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022 የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ የሚል ሽልማት አሽነፈ።
ግሎባል ትራቭል ማጋዚን 'ትሬዚስ አዋርድ' በሚል በሚያዘጋጀውና ከደንበኞች በሚሰበሰብ ድምጽ በሚካሄድ ውድድር ነው አየር መንገዱ አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ ያገኘው።
አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ መሆኑን ትራዜስ ትራቭል ጽፏል። ድምጻቸውን ለአየር መንገዱ የሰጡ ወገኖች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመስግነዋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-26
