የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀርስ ሲደርሱ እንዳሉት ግዜው በቀኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ ግፎችን ብቻ ማስታወሱን ትተን ለተሻለ ነገ የምንሰራበት ነው ብለዋል።
በግዜው የተፈጸሙ ግፎችን እንዲያጣራ ከሁለቱም ሀገራት በተውጣጡ የታሪክ አጥኚዎች የተቋቋመው ቡድንም ውጤታማ ለውጥ እያመጣ እንደሆነ ገልጸዋል።
የአልጄሪያ አቻቸው አብዱልማዲጅድ ታቦኔ የማርኮን ጉብኝት የሻከረውን የሁለቱ ሀጋራት ግንኙነት ዳግም እንደሚያድሰው ተናግረዋል።
አልጄሪያ ለ130 ዓመት በፈረንሳይ ቅኝ ተገዝታለች።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-26
