ሀገሬ ቲቪ

የኢራንና አሜሪካ የኒውክሌር ስምምነት

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተጀመረው የኒውክሌር ስምምነት የሚሰምር ከሆን የዓለም የነዳጅ ዋጋን ወደ 80 ዶላር ዝቅ ያደርገዋል ተባለ።

በጎጎሮሳዉያኑ 2015 ተቋርጧ የነበረው የኒውክሌር ድርድር መጀመሩና ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየቱ እየተገለጸ ነው።

የተባበሩት መንግስታት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር መፈተሽን ጨምሮ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ስምምነት ከተደረሰ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ ትልቅ ለውጦችን ያመጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ሁሉም የምዕራባውያን ማዕቀቦች እንደተነሱ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ኢራን በቀን ከ 7ሺሕ -8ሺሕ በርሜል ተጨማሪ ምርት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች መላክ ትችላለች ሲል ሲጂቲኤን ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-26