ሀገሬ ቲቪ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአልጀርስ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአልጀሪያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በአልጀርስ የሚገኘውን የሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም መጎብኘታቸው ተሰማ።

የሰማዕታት መታሰቢያው አልጀሪያ 20ኛ ዓመት የነጻነት በዓሏን ስታከብር ለአገሪቷ ነጻነት የህይወት መሰዋዕትነት የከፈሉ ዜጎችን ለማሰብ የተሰራ መሆኑ ይታወቃል።

ትናነትና ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አልጀሪያ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አብዱል መጅድ ታቡኔ ጋር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በሚያድግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-29