ሀገሬ ቲቪ

ፓኪስታን በጎርፍ አደጋ እየተናጠች ነው

በፓኪስታን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ1,033 በላይ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

የሀገሪቱ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ባለስልጣን በትንሹ 33 ሚሊዮን ሰዎች በአደጋው ተጎድተዋል ነው ያለው ። ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታዩት አስከፊ ነው በተባለው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ዜጎች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናትም ይገኙበታል ።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-29