ጃፓን ለአፍሪካ በቀጣዮቹ 3 አመታትም የ30 ቢሊየን ዶላርም ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች ።
የቶኪዮ ዓለም አቀፍ ትብብር ለአፍሪካ ልማት 8ኛውን ጉባኤ በቱኒዚያ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው ላይ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበረ የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የጃፓን አፍሪካ ጥምረት በትምህርት በጤና በግብረናና በውሃ ዘርፍ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።
30 የአፍሪካ ሀገራት በመሪ ደርጃ በተወከሉበት በዚህ ጉብዔ ጃፓን ለአህጉሪቱ ልማት ከምታደርጋቸው ድጋፎች በተጨማሪ የኢንቭስትመንት አቅሟን ለማሳደግ በምትችልበት ጉዳይ ላይ ውይይት ተደረጓል።
የቶኪዮ ዓለም አቀፍ ትብብር ለአፍሪካ ልማት ከተመሰረተ 30 ዓመት ቢሆነውም ቻይና በአፍሪካ እየፈጠረችው ካለው ተጽኖ አንጻር ጃፓንን ተውዳዳሪ አላደረጋትም በሚል ይተቻል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-08-29
