በዩክሬን ዛፖሪዥያ በተሰኘው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ የደረሰውን ጉዳት ላይ በዚህ ሳምንት ምርመራ ይካሔዳል ተባለ።
ሩሲያና ዩክሬን በጣቢያው አካባቢ የተፈጸምውን ጥቃት እኔ አልፈጸምኩትም በሚል እርስ በእርሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት በበኩሉ ሩሲያ ይዛ የምትገኘውን የዩክሬን የኒውክሌር ማመንጫ ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውቋል።
የተቋሙ ዋና ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ እንደተናገሩት በዛፖሪዥያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አቅራቢያ የደረሰውን ጉዳት እናጣራለን ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም "የዩክሬንን እና የአውሮፓን ትልቁ የኑክሌር ተቋም ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ አለብን" ማለታቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-29
