ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት ሚሊዮን ዜጎቼን የኮሌራ ክትባት ለመከተብ ተሰናድቻለሁ አለች፡፡ በሀገሪቱ የኮሌራ ወረርሽኝ መከስቱን ተከትሎ ነው ይህ የተገለጸው፡፡ ክትባቱ ከአንድ አመት የዕድሜ ክልል ጀምሮ ላሉ ዜጎች ይሰጣል መባሉ ተሰምቷል፡፡ በወረርሽኙ ተጋላጭ በሆኑ ሶስት ግዛቶች ክትባቱ የሚሰጥ ሲሆን በአስራ ሦስት የጤና ዞኖችም ተደራሽ ይሆናል፡፡ ለስድስት ቀናት ይቆያል በተባለው የክትባት ዘመቻ 3ሺሕ የጤና ባለሙያዎች ተሰማርተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ተመሳሳይ የክትባት ዘመቻ ተደርጎ ከ1ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መከተባቸው ይታወሳል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው በፈረንጆቹ አመት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 1መቶ ሀምሳ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ8 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ተይዘው እንደነበር የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ ኮሌራ በሽታ ንጽህናው ያልተጠበቀ ውሀ እና ምግብ በመጠቀም እና በመጠጣት ሊከሰት የሚችል የጤና እክል ነው፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-28
