የአዲስ አበባ የግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የመንገድ ላይ ማስታወቂያን የሚመለከት መመሪያ አዘጋጀሁ አለ። ይህ የተነገረው ተቋሙ በ2014 ዓ.ም. ያከናወናቸውን ስራዎች በተመለከተ ምክክር ባካሄደበት ነው ።
የተዘጋጀው መመሪያ አንድ የማስተዋቂያ ቋሚ ላይ ሁለት ማስታወቂያዎችን በሁለቱም አቅጣጫዎች የሚሰቀሉበትን መንገድ ይፈጥራል ተብሏል። የአዲስ አበባ የግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣኑ ከተለያዩ አገልግሎችቶች 60 ሚሊዮን ብር አግኝቻለሁ ብሏል።
ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር የሚጠይቀው ክፍያ ዝቀተኛ ነው ያለው ባለስልጣኑ ማሻሻያ በማድረግ በቀጣይ 156 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዷል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-08-30
