ወደ ጅቡቲ የደርስው ስንዴ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ለኢትዮጵያ የተላከ ነው ። ይህም ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ የተላከ ነው።
ጂቡቲ የደረሰችው መርከብ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአለም ምግብ ፕሮግራም የተገዛውን 23 ሺህ ቶን ስንዴ ይዛለች ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ክሌር ኔቪል እንደተናገሩት ስንዴው በጦርነት እና በአስከፊ ድርቅ ምክንያት የተጎዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-08-30
