ሀገሬ ቲቪ

ራይላ ኦዲንጋ የፍርድ ቤትን ውሳኔ አከብራለሁ አሉ

በኬንያ በተካሄደው ምርጫ ውጤቱን አልቀበልም በሚል ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት ዋነኛ ተፎካካሪው ራኢላ ኦዲንጋ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ምንም ይሁን ምን እቀበላለሁ ብለዋል።

የ 77 አመቱ ራኢላ ኦዲንጋ ለ 5ተኛ ግዜ በተፎካከሩበት ምርጫ ከ2 በመቶ ባነሰ ድምጽ በዊሊያም ሩቶ መሸነፋቸው ይታወሳል። ውጤቱን ያልትቀበሉት ኦዲንጋም 72 ገጽ አቤቱታቸውን ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ አቅርበው ውጤቱን እየተጠባበቁ ነው።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ማለታቸው ሀገሪቱን ከብጥብጥ ይታደጋል በሚል ብዙ ኬንያውያን እፎይታ ተሰምቷቸዋል። ፍርድ ቤቱ የራይላ ክስ አሳማኝ ሆኖ ካገኘው ምርጫው በ60 ቀን ውስጥ ይደገማል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-08-30