ሀገሬ ቲቪ

ቦትስዋናን የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ የሚያስችላት ፕሮጀክት

ቻይና በቦትስዋና የገነባቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ቦትስዋናን ኃይል ወደ ውጭ መላክ የሚያስችላት ነው ተባለ። ቦትስዋና ባለፉት ዓመታት ዋና የኤሌክትሪክ ኃይል አስመጪ በመሆን ነበር የምትታወቀው።

በቻይና ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተገነባው ሞርፑል ቢ የተሰኘው ድንጋይ ከሰል ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ቀስ በቀስ የቦትስዋናን ገጽታ እየቀየረ ነው ሲሉ በቦትስዋና ዩኒቨርሲቲ የምሕንድስና እና ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር ኤድዋርድ ዲንትዌ ተናግረዋል።

ይህም ሀገሪቱ ን የኤለክትሪክ ኃይል ገዢ ከመኾን ወደ መሸጥ የሚለውጣት ነው ብለዋል። ላለፉት ሶስት ወራት ሞርፑል ኤ እና ቢ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ጀምረዋል። በሰዓት ከ 800 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ወደ ብሔራዊ መስመር በመላክ ላይ ናቸውም ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-08-30