እጅግ ጥንቃቄን የሚሹ ልንጠብቃቸው ግዴታ ያለብን የገዛ አብራኮቻችን ክፋዮች ናቸው፤ ሕፃናት። መቼ፣ የቱ ጋር፣ ምን እንደሚያጋጥመን አናውቀውም እና ከሚመጣው ነገር ሁሉ በቻልነው አቅም ሁሉ እንጠብቃቸዋለን።
ታዲያ ይህንን ሁሉ ነገር ፉርሽ ያደረገ የ10 ዓመት ታዳጊ ወዲህ አለ መባሉን ሰማን። የአሜሪካዋ ኦኮሃማ ግዛት ነዋሪ የሆነው ታዳጊ የእናቱን ነብስ ማዳን በመቻሉ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆኗል።
ጋቪን ኬኒ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ባለ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ስትዋኝ የነበረችው እናቱ ድንገት እየሰጠመች መሆኗን ከተመለከተ በኋላ የወሰደው እርምጃ በርካቶችን አስደምሟል።
ኢፕሊፕሲ ወይም በወል መጠሪያ የሚጥል በስታ ታማሚ የሆነችው የኬኒ እናት በመዋኘት ላይ እያለች ድንገት ይጥላታል ይህንን የተመለከተው ልጅ ኬኒ አልተደናገጠም፤ በፍጥነት ወደ መዋኛው ገብቶ እናቱን ጎትቶ አውትቷታል።
በቅርቡ የነበሩት አያቱ ቀጥለው በመድረስ ለኬን እናት እርዳታን አድርገውላታል። ይህ ተግባሩም እንዴት ያለ ልባም ጀግና ነው አሰኝቶታል።
ታዳጊው ሁኔታውን እንዲህ ያስታውሰዋል።
“ውሃው ሲንቦራጨቅ እና ሲፈናጠር ሰማሁ፤ የመስጠም አይነት ነገር ተመለከትኩ እናቴ ነበረች እና ፈጥኜ ወደ መሃና ገንዳው ገባሁ እና ወደ መወጣጫው አስጠጋዋት።”
ታዳጊው ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ የመለሰው ነበር።
“እጅግ በጣም አስገራሚ ነገር ነው። እንዲህ ያሉ የድርጊት ነገሮች ላይ አይቼውም አላውቅም፤ ይህንን ሳይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው። በቤት ውስጥ በነበረው የደህንነት ካሜራ አማካኝነት ነው ያየሁት። በጅግ በጣም ኮርቼበታለው፤ ነገር ኝ በሱ በኩል ይህንን ማየት ልብን የሚሰብር ነገር ነው።”
ሌሪ ኬኒ ነብሷን ያዳነላት ታዳጊ እናት ነች ይህንን ያለችው።
ነገሩ የከተማዋን የፖሊስ መኮንኖች ልብ ያሚቀም ነበር። ጀኛችን ነህ ሲሉም በተማሪ ጓደኞቹ ፊት ሽልማትን አበርክተውለታል። ሰዎችን የመርዳት ፍላጎት እና ሃሳቡ በእጅጉ የሚመሰገን ነው ስትል እናት ተደምጣለች።
በሳምሶን ገድሉ
2022-08-30
