ሀገሬ ቲቪ

ያለ ማስያዣ ብድር ሊሰጥ ነው

የኢትዮጵያ ባንኮች በአነስተኛ ደረጃ ያሉ ዜጎችን ያለማስያዣ ብድር መስጠት ላይ ክፍተት አለባቸው ሲባል ይሰማል። በማስያዣ እንኳን ቢገኝ ወለዱ አይቀመስም ።

የብሄራዊ ባንክ መረጃ ስንመለከት በ2021 በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች ከሰጡት 300 ቢሊዮን ብድር ውስጥ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙና ማስታዣ ማቅረብ ለማይችሉ 5 ቢሊዮን ብቻ እንደሰጡ ይገልጻል።

ባንኮቹ ለሚሰጡት ብድር 3 እጥፍ ማስያዣ መጠየቃቸው ደብተር ከማውጣት ያለፍ ብድር እንዳይበደሩ አድርጓቸዋል ተብሏል።

ንብረት በመያዝ የተመሠረተውን የኢትዮጵያን የብድር አሰጣጥ በመቀየርና ውስን ሆኖ የቆየውን የተበዳሪዎች ቁጥር ትርጉም ባለው መልኩ ከፍ ማድረግ ከመንግስት ይጠበቃል ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ።

አቶ ተመስገን ዘለቀ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አካታችነት ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው።

ሀላፊው ብሄራዊ ባንክ የተንቀሳቃሽ ንብረት ምዝገባ ስርዓት እንደሚዘረጋ ነግረውናል። አዋጁ አይምሮዋዊ ንብረቶችን ማስያዝ, ተቋማት ያላችውን ማሽነሪዎችን ማስያዝ ጨምሮ ሌሎችም ጥቅሞች እንደሚኖሩት ነግረውናል።

ከተወሰኑ ተቋማት ጋር አብርን ለመስራት አቅደናል ያለው ባንኩ በበተመረጡ ክልሎች ስርዓቱን ለመተግብር ተዘጋጅቻለሁ ብሏል በኢትዮጵያ ከሚሰጠው ብድር ከ85 በመቶ በላይ ከተሞች ላይ ያተኮረ መሆኑን መረጃዎች ያሳይሉ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-31