በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ዋግና ወልቃይትን ጨምሮ በሱዳን ድንበር አከባቢ “ወረራ” ከፍቷል ተባለ።
ቡድኑ የጥቃት ቦታዎቹን በማስፋት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አከባቢ “ወረራ” ከፍተዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
ይህንን የህወሓት ወረራ የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ እንደሚገኝም በመግለጫው ተጠቁሟል።
በተጨማሪ በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም ብሏል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው መግለጫ ።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-31
