ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ወታደራዊ ዩኒፎርም ማምረት ጀመረ። እነዚህን የጸጥታ ኃይል የደንብ ልብሶችን በፓርኩ ኢፒክ አፓረል የተሰኘው ኩባንያ ከሁለት ሳምንት በፊት ማምረት ጀምሯል።
ከዚህ ቀደም የደንብ ልብስ በሃገር ዉስጥ ማምረት በመጀመሩ ሀገሪቱ ታወጣ የነበውን 60 በመቶ የውጪ ምንዝሬ እንዳስቀረላት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መናገሩ ይታወሳል።
የመከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል የደንብ ልብሶችን ማምረት የጀመረው ኢፒክ አፓረል የተሰኘው ኩባንያ ከ 177 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ የጀመረ አምራች ድርጅት ነው።
በሙሉጌታ በላይ
2022-08-31
