ሀገሬ ቲቪ

የዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስጠንቀቂያ

የዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በአፍሪካ የጠፉ ህጻናት ቁጥር ከ25 ሺህ በላይ ሆኗል።ኮሚቴው ይህንን ያለው የዓለም ዓቀፍ የመጥፋት ቀን አመልክቶ ባወጣው መረጃ ነው ።

ለእንዲህ ዓይነቱ መሰወር ከሚዳርጉ ጉዳዮች መካከል የጸጥታ እጦት አንዱነው ሲል አፍሪካን ኒውስ ጽፏል።በአህጉሪቱ ከ35 በላይ የትጥቅ ግጭቶች እንዳሉ በመረጃው ተጠቅሷል።

ይህም በሺዎችየሚቆጠሩ ሰዎች ከነዚህ ግጭቶች ርቀው አስተማማኝ ቦታን ፍለጋ ህጻናትንጨምሮድንበሮችን፣ የሰሃራ በረሃ እና የሜዲትራኒያንን ባህር እንዲሻገሩ አድርጓል።በየትኛው የአፍሪካ ሀገራት የጠፉ ዜጎች ቁጥር እንደሚያል መረጃው ያለው ነገር የለም።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-31