ሀገሬ ቲቪ

ዳንጎቴ የናይጄሪያን የውጭ ምንዛሬ ለማዳን እየሰራ ነው

ዳንጎቴ ስኳር ፋብሪካ ወደ ናይጄሪያ የሚገቡትን የስኳር ምርቶች በ40 በመቶ ቀንሷል ተባለ።ፋብሪካው ከ30,000 በላይ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት ሀገሪቱን ከውጭ ምንዛሪ እጥረት አድኗል ነው የተባለው ።

አዲስ የተገነባው የስኳር ፋብሪካው በአፍሪካ ትልቁ መሆኑ ተነግሯል።በዓመት 430,000 ቶን የተጣራ ነጭ ስኳር የማምረት አቅም አለው ተብሎለታል ።ናይጄሪያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 1.8 ቢሊዮን ዶላር ለስኳር ግዢ ማውጣቷ በመረጃው ተጠቅሷል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-08-31