50ሺ የቻይና ወታደሮች ለወታደራዊ ልምምድ ሞስኮ መድረሳቸው ተሰምቷል። በሩሲያ የተለያዩ ግዛቶች ለ7 ቀናት በሚካሄደው የሁለቱ ሀገራት ጥምር ወታደራዊ ልምምድ 5ሺ የጦር መሳሪያ አይነት ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል።
140 የጦር አውሮፕላኖችና 60 የጦር መርከቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑም የሩሲያ መከላኪያ ሚንስቴር አስታውቋል።ወታደራዊ ልምምዱ ከምዕራባውያን ጋር ያለ እሰጣ ገባ ካየለ መቋቋም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሎለታል።
በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ፣ ሞንጎሊያ እና ሌሎችን ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-08-31
