ሀገሬ ቲቪ

ሩሲያ ወደ አውሮፓ የተዘረጋውን የጋዝ ማስተላለፊያ ሙሉ ለሙሉ ዘጋች

ሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በርካታ ሀገራት በተለይም ምዕራባውያን ከዩክሬን ጎን ቆመው ሩሲያ እየፈጸመች ያለችው “ወረራ” ነው ሲሉ ከድርጊቷ እንድትታቀብ ብዙ ሲያሳስቡ ቆይተዋል እያሳሰቡም ይገኛሉ።

የአውሮፓ ሀገራት ዋና የነዳጅ እና የጋዝ አቅራቢ የኾነችው ሩሲያም ምላሿን ወደ እነዚህ ሀገራት በምታስገባው የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ ላይ አድርጋለች።

ሲያሻት በራሴው መገበያያ ሩብል ነው የምሸጠው ስትል፤ ሲያሻት ደግሞ ወደ አውሮፓ የተዘረጉትን የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን እየዘጋች እና እየከፈተች በነዳጅ እጥረት እንዲታመሱ እያደረገቻቸው ትገኛለች።

አሁንም ታዲያ በተመሳሳይ ወደ አውሮፓ በዋናነት ደግሞ ወደ ጀርመን የሚወስደውን ዋና የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ሙሉ ለሙሉ መዝጋቷ ተሰምቷል።

መስመሩ ጥገና ያስፈልገዋል የሚል ምክንያት አቅርባለች። የሩሲያ ግዙፉ የጋዝ ኩባንያ ጋዝፕሮም በኖርድ ማስተላለፊያ መስመር አንድ በኩል የተጣለው ገድብ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ይቆያል ብሏል።

በሐምሌ ወር ይኸው ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ለ 10 ቀናት ተዘግቶ ቆይቶ እንደነበር ቢቢስ በዘገባው አስታውሷል። ሩሲያ በፊትም ቢኾን ወደ አውሮፓ የምትልከውን ጋዝ እንደቀነሰች ይነገራል።

በዚህ እርምጃዋም የኃይል አቅርቦትን በምዕራባውያን አገሮች ላይ እንደ ጦር መሣሪያ አድርጋ እየተጠቀመች ነው የሚል ክስ ይቀርብባትል ምንም እንኳን እሷ ባትቀበለውም።

በ2003 ዓ.ም. የተሰራው ኖርድ የተሰኘው ጋዝ ማስተላለፊ መሥመር 1,200 ኪሎ ሜትርን ርዝማኔ ያለው ነው። በቀን 170 ሚሊዮን ኪውቢክ ሚውትር ጋዝ ከሩሲያ ወደ ጀርምን ይተላለፍበታል።

ይሁን እንጁ መስመሩ ባጋጠመው ብልሽትካለው አቅም እየሰራ ያለው 20 በመቶውን ነው ስትል ሩሲያ በቅርቡ መናገሯ ይታወሳል ስለዚህም ጥገናው አስፈላጊ ነው ብላለች። ጀርመን በበኩሏ ግድየለም በጥገና ምክንያት የሚላከው ጋዝ ቢቀንስም መቋቋም እችላሉ ብላች።

የጀርመን ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሮበርት ሀቤክ ግን የጀርመን ኢኒዱስትሪዎች ለልማት የሚያደርጉትን አስተዋስጻኦ የሚጎዳ ነው ብለዋል። ሚኒስትሩ ምርታቸው እንዲቀንስ ያደርጋል ሲሉ ለፋይናኒሺያል ታይምስ ተናግረዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ ሮበርት ሀቤክ ሩሲያ እንደምትለው በጋዝ ማስተላለፊያዎቹ ላይ የደረሰ ምንም አይነት ችግር የለም ውሸት ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

የአውሮፓ መሪዎች ሩሲያ የጋዝ ዋጋን አሁን ካለበትም በላይ ከፍ ልታደርገው ትችላለች የሚለው ስጋታቸው አልተቀረፈላቸውም። የአውሮፓ ኀብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዶር ሌየን በበኩላቸው በዚህ የጋዝ ምርት ላይ ጥገኛ መኾን ነው ስጋታችንን ሊቀርፍልን የሚችለው ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የሚያተኩር አዲስ የኢኮኖምክ ሞዴል ልንፈጥር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ሩሲያ ግን የነዳጅ ንግዷን ከአውሮፓ ወደ ቻይና ያዞረች ይመሰላል ለዚህ ማሳያው በቅርቡ በወጣ ሪፖርት ባለፉት ቻይና ከሩሲያ የምታስገባው ነዳጅ ከእጥፍ በላይ ማደጉን አሳይቷል እና።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-01