ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደርጉ አምባሳደሮች እና ዲፐሎማቶች በሰሞኑ በአሽባሪነት በተፈረጀው ህወሓት ወረራ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚንስትሩ በንግግራችው መንግስት ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፈታት ጥረት ቢያደርግም የህወሓት ቡድን ግን ለ 3ተኛ ገዜ በህዝባዊ ማዕበል ጦርነት ከፍቶል ብለዋል ።
በዚሀም ወረራ በአማራ እና በ አፋር ክልሎች ላይ ዜጎች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደርሰ መሆኑን አስረድተዋል ።
ህወሃት እነዚህ ህዝቦች ላይ ዳግመኛ በደል እንዳያደርስ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።
መንግስት አሁንም የሰላም አማራጩ በር አለመዝጋቱን ገልጸው ነገር ግን የሃገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣም አስታውቀዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-01
