ሀገሬ ቲቪ

“የሰላም ቅደመ ሁኔታው ሰላም ብቻ ነው!!” የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በፌዴራል መንግስትና በሕወሓት መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።

ጉባኤ ይህንን ያለው “የሰላም ቅደመ ሁኔታው ሰላም ብቻ ነው!!” በሚል መርህ ባወጣው መግለጫ ነው ።ጉባኤው ጦርነቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከሀገር ሽማግሌ መማክር ጉባኤ፣ ከታዋቂና ተሰሚነት ካላቸው ገለልተኛ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት በሰላማዊና በምክክር እንዲፈታ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ችግሩን በወቅቱ ለማረምና ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ መቅረቱን አስታውሰዋል። የህወሓት ቡድን በድጋሜ ወደ ጦርነት መግባቱን አውግዘዋል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-09-01