ሀገሬ ቲቪ

ከ500ሺሕ በላይ ናይጄሪያውያን በጎርፍ ጉዳት ደረሰባቸው

በናይጄሪያ በጎርፍ ሳቢያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቅላችውን የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት አስታወቁ ።

መሐሙዱ ቡሃሪ ከ20 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ነው የተባለው ከባድ ዝናብ በ36ት ግዛቶች ላይ አደጋ መደቀኑን ገልጸዋል። በጎርፍ ሳቢያ 270 የሚሆኑ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደርሰባቸውም ተነግሯል።

እስካሁን ግን ጎርፉ ዜጎችን ለሞት መዳረጉን የተመለከተ መረጃ አለመኖሩን አፍሪካ ኒውስ ጽፏል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-09-01