ወረራ በተፈጸመበት የአፋር ክልል የማምረቻ ተቋማት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአፋር ሦስት ዞኖች የማምረቻ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ቡድን ልኳል፡፡ በማምረቻ ፣ በንግድ ፣ በሌሎችም ተቋማት እና መሠረተ ልማቶች ላይ ዝርፊያ እና ውድመት ተፈጽሟል፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው የማምረቻ ተቋማት ውስጥ አንዱ አሳድ ዱቄትና መኮሮኒ ፋብሪካ መሆኑን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በአሸባሪነት የተፈረጀው የህውሓት ቡድን ባደረሰው ጉዳት ምክንያት በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ የማምረት ሂደት ሙሉ በሙሉ መስተጓጎሉን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡ ቡድኑ አከባቢውን ተቆጣጥሮ በቆየባቸው ቀናት ድርጅቱ ለምርት ግብዓትነት የሚጠቀምባቸውን ጥሬ ዕቃዎች እንዲሁም የተመረቱ ምርቶች ተዘርፈዋል ፤በማሽኖች ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ መንግስሥት የጉዳቱን መጠን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ችግሩን የሚመጥን መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል፡፡ በእነዚህ ማምረቻ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ስራ አጥ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-28
