ሀገሬ ቲቪ

በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ስዎች ቁጥር ከ50000 ደረሰ

የዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ስዎች ቁጥር 50 ሺ መደረሱን አስታወቀ ። 16 ሰዎችም በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።

የዓለም ጤና ድርጅት በሐምሌ ወር ነበር የዝንጀሮ ፈንጣጣን ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ነው ሲል ያወጀው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚተላለፈው መንኪፖክስ በተባለ ቫይረስ አማካይነት ሲሆን፥ ለፈንጣጣ በሽታ ከሚያጋልጠው ቫይረስ ጋር ተዛማጅነት አለው።

በመቅደስ እንዳለ
2022-09-01